Meet the spiritual leaders and ministry team of Baziliya International who are committed to serving God's people with integrity, wisdom, humility, and vision.
በትክክለኛነት፣ በጥበብ፣ በትሑትነት እና በራዕይ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማገልገል የተዋጁ የባዚልያ ኢንተርናሽናል መንፈሳዊ አመራሮችን እና የአገልግሎት ቡድን ይተዋወቁ።
Pastor's Wordየፓስተሩ ቃል
Monthly Message — Sonship
የመጋቢው መልእክት — ልጅነት
We are children of God. Sonship is not a change obtained through religious systems, but the divine mystery of being born from heaven.
Sonship is our heavenly identity and spiritual nature — not something defined only by the routines of life.
Sonship is the mystery of being born for the Father's will: a life that transcends time, place, and circumstance; making Him the foundation of our existence and the law of our movement.
A child has no will of his own. A child is born for the Father's will — and eternity is living for the Father's will.
Sonship is not religious tradition, a system to perform, an inheritance of soul-vision, name, fame, or a discourse of glory. Rather, it is the mystery of rising from death to sin and being transformed in righteousness.
The spirit of sonship is known through childlikeness, humility, gentleness, and serving all — carrying the wood Isaac was bound on, carrying the cross Christ was crucified on, through obedience, submission, and transformation by faith.
The child does not live in wonders. God lives in him. In sonship there is service, not reign.
The child's focus is not personal greatness, knowledge, or earthly authority, but faithfully serving the Father who sent him — seeing Him in all things.
So let us rise to faithfully serve the Father who called and sent us. Let us remember we are called not to establish our own kingdoms, but to advance God's kingdom.
Understanding the Gospel of the Kingdom revealed to us in this age of grace, with humility, obedience, and loving one another, let us work to expand the kingdom as sons and daughters of God.
This is our church's message and call.
እኛ የእግለዚአብሔር ልጆች ነን። ልጅነት በሃይማኖታዊ ሥርዓት ለውጥ የሚገኝ ሳይሆን ከሰማይ የመወለድ አምላካዊ ምስጢር ነው።
ልጅነት በሕይወት ሥርዓታችን ብቻ የሚተረጎም ሰማያዊ መልካችን ፣ መንፈሳዊ ማንነታችን ነው።
ልጅነት ለአብ ፈቃድ የመወለድ ምስጢር ፣ በጊዜ ፣ ቦታ እና በሁኔታ ሳይወሰኑ አብን የማተለቅ ሕይወት ፣ አብን የሕልውና መሠረትና የእንቅስቃሴ ሕግ ማድረግ ነው።
ልጅ የራስ ፈቃድ የለውም። ልጅ ለአባት ፈቃድ ተወልዶ ለአባት ፈቃድ የመኖር ዘላለማዊነት ነው።
ልጅነት ሃይማኖታዊ ወግና ሥርዓት ማስፈጸሚያ ፣ የነፍስ ርዕይ ማትረፊያ ፣ ስም ፣ ዝናና ክብር መሸመቻ ዲስኩር አይደለም።
ይልቁንስ ለኃጢአት መሞትና በጽድቅ ለመመላለስ የመነሣት ምሥጢር ነው።
የልጅነት መንፈስ በታናሽነት ፣ በትህትና በየዋህነት እና ሁሉን ለማገልገል እንደ ይስሐቅ የሚቃጠልበትን እንጨት ፣ እንደ ክርስቶስ የሚሰቀልበትን መስቀል ተሸክሞ በመታዘዝ፣ በመገዛትና በእምነት በመመላለስ ይታወቃል።
ልጅ በተአምራት አይኖርም። እግዚአብሔር ግን በእርሱ ይኖራል። በልጅነት ማገልገል እንጂ መንገስ የለምና።
የልጅ ትኩረት የላከውን አብን በታማኝነት ፈቃዱን በማገልገል እርሱ በሁሉ ነግሶ ማየት እንጂ የግል ታላቅነት ፣ እውቅና ወይም ምድራዊ ስልጣን ከቶ አይሻም።
እንግዲህ እኛም የጠራንንና የላከንን አብን በታማኝነት ፈቃዱን ለማገልገል እንነሳ። የተጠራነው የራሳችንን መንግስታት ለመመስረት ሳይሆን የእግዚአብሔርን መንግስት ለማራመድ ነውና እናስተውል።
በተሰጠን ስፍረ-ዘመን የተገለጠልን የመንግሥቱን ወንጌል በመረዳት በትህትና ፣ በመታዘዝና እርስ በርሳችን በፍቅር በመያያዝ እንደ እግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ለመንግሥቱ መስፋት እንስራ።
ይህ የቤተ-ክርስቲያናችን መልዕክትና ጥሪ ነው።
Your brother, Dr. Bisrat Tadele
ወንድማችሁ ብሥራት ታደለ (ዶ/ር)